ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም. አ.ማ. አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሄደ፡፡
ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም. አ.ማ.
አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሄደ፡፡
ተቋሙ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በዉቢቷ ባህርዳር ከተማ ሙሉዓለም የባህል ማዕከል አዳራሽ የ3ኛ መደበኛ ጉበኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡ ጉባኤዉ የብሔራዊ ባንክ
እና የሰነዶች ማረጋገጫ ታዛቢዎች በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ተካሂዷል፡፡
ጉባኤዉን የመሩት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ይልቃል ሞኘ የጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና
መጣችሁ ካሉ በኋላ ጉባኤዉን ማካሄድ የሚያስችል ድምጽ መገኘቱ ተረጋግጦ
ጉባኤዉን አስጀምረዋል፡፡ ሰብሳቢዉ የተቋሙ ስራ አመራር ቦርድ አባላት በበጀት አመቱ ያከናወኗቸዉን ዋና ዋና ተግባራት እና በተቋሙ
በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተከናወኑትን አበይት ተግባራት አብራርተዋል፡፡ ሰብሳቢዉ አያይዘዉም በዚህ ፈታኝ በሆነ የኢኮኖሚና ሁኔታ
ላይም ሆነን ተቋሙ ከባለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት በተሻለ ተግባራትን በማከናወን በተነፃፃሪነት የተሻለ ትርፍ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
የገለልተኛ ኦዲተር ሪፖርት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ባለአክሲዩኖች በዘጠኝ (9) አጀንዳዎች ላይ
በስፋት ከተወያዩ በኋላ በገለልተኛ ኦዲተሩ ሃሳብ ተሰጥቶባቸዉ ዉሳኔዎችን
በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል፡፡
በመጨረሻም የተቋሙን ካፒታል ለማሳደግ
ስትራቴጅካዊ ማስፈጸሚያ ስልቶች ተቀምጠዉለት ከፒታሉን በአጭር ጊዜ ማሳደግ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባኤዉ ተጠናቋል፡፡